top of page
bible.jpg

Upholding the Protestant conviction of Sola Scriptura (“Bible only”), these 28 Fundamental Beliefs describe how Seventh-day Adventists interpret Scripture for daily application.

blue-geometric-shapes-4k.jpg
blue-geometric-shapes-4k.jpg
blue-geometric-shapes-4k.jpg

የሰባተኛው ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን  መሠረታዊ እምነቶች

blue-geometric-shapes-4k.jpg
blue-geometric-shapes-4k.jpg
blue-geometric-shapes-4k.jpg

1. የእግዚአብሔር ቃል

መጽሐፍ ቅዱስ ፣ ማለትም ብሉይና አዲስ ኪዳናት ፣ የእግዚአብሔር ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተመር ተው የተናገሩት እና የጻፉት በመለኮታዊ መገለጥ የተሰጠ የእግዚአብሔር ቃል ነው፡፡ በዚህ ቃል ውስጥ
እግዚአብሔር ለደህንነት አስፈላጊ የሆነ እውቀትን አስቀምጧል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ስህተት የሌለበት የፈቃዱ መገለጫ (መገለጥ) ነው፡፡ በመሆኑም መጽሐፍ ቅዱስ የትክክለኛ ባህሪ መለኪያ ፣ የልምምድ ሁሉ መፈተኛ፣ አስተምሮን በአምላካዊ ስልጣን የሚገለጥ ፣ እና ሊታመን የ ሚገባው በታሪክ ውስጥ የእግዚአብሔር ስራ ዘገባ ነው፡ ፡ (2ጴጥ.1፡ 20፣ 21፣ 2ጢሞ.3፡ 16፣ 17፣ መዝ.119፡ 105፣ ምሳ ሌ.30፡ 5፣ 6 ኢሳ .8፡ 20፣ ዮሐ.17፡ 17፣ 1ኛ ተሰ . 2፡ 13፣ እብ.4፡ 12)፡ ፡

2. ሥላሴ

አንድ እግዚአብሔር አለ ፡ - አብ ፣ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ ፣ የሶስት ዘላለማዊ የሁኑ አካሎች አንድነት፡፡ እግዚአብሔር የማይሞት፣ ሁሉን ቻይ፣ ሁሉን የሚያውቅ ፣ ከሁሉ በላይ የሆነና በሁሉም ቦታ የሚገኝ ነው፡፡ እርሱ መጨረሻ የሌለውና ከሰብዓዊ ማስተዋል በላይ ነው፣ ነገር ግን እርሱ ራሱን በመግለጡ ይታወቃል፡ ፡ እግዚአብሔር - ፍቅር የሆነ - እርሱ ፍጥረ ት በሙሉ ለዘላለም ሊያመልከው ፣ ሊሰግድለትና ሊያገለግለው የሚገባ ነ ው፡፡ ( ዘ ዳ. 6፡ 4፣ ማቴ.28፡ 19፣ 2ቆ ሮ. 13፡ 14፣ ኤፌ. 4፡ 4-6፣ 1ጴጥ. 1፡ 2 ፣ 1ጢሞ. 1፡ 17፣ ራዕ ይ 14፡ 7)፡ ፡

3 . እግዚአብሔር አብ

ዘላለማዊ አባት እግዚአብሔር የፍጥረት ሁሉ ፈጣሪ ፣ ምንጭ፣ መጋቢና የበላይ ገዥ ነው፡ ፡ እርሱ ጻድቅና ቅዱስ ፣ መሐሪ ና ባለጸጋ፣ ለቁጣ የዘገየ ና በጽኑ ፍቅር ና ታማኝነት የተሞላ ነው፡፡ እነዚህ በልጁና በመንፈስ ቅዱስ የታዩት ችሎታዎችና ኃይል የአብም መገለጫዎች ናቸው፡ ፡ ( ዘ ፍ. 1፡ 1፣ ዮሐ. 3፡ 16፣ 1ዮሐ. 4፡ 8፣ 1ጢሞ. 1፡ 17፣ ዘ ፀ .34፡ 6፣ 7፣ ዮሐ. 14፡ 19)፡ ፡

4. እግዚአብሔር ወልድ

እግዚአብሔር ዘላለማዊ ወልድ በኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋ ለባሽ ሆነ፡፡ በእርሱ ሁሉም ነገሮች ተፈጥረዋል፣ የ እግዚአብሔር ባህርይ ተገልጦአል፣ የሰብአዊ ዘር ደህንነት ተፈጽሞአል፣ ዓለምም ተፈርዶበታል፡ ፡ እርሱ

በመንፈስ ቅዱስ ተፀንሶ ከድንግል ማርያም ተወልዶአል፡ ፡ እንደ ሰብአዊ ፍጡር ኖሮ ፈተናን ተለማምዶአል፣ ነገር ግን የእግዚአብሔርን ጽድቅና ፍቅር በትክክል አሳይቶአል፡፡ በተአምራቶቹ አማካይነት የእግዚአብሔር ኃይል ስላሳየ ቃል የተገባው የእግዚአብሔር መሲህ መሆኑ ተረጋግጦአል፡፡ ስለ ኃጢአቶቻችን በፈቃደኛነት በመስቀል ላይ መከራ በመቀበል ለእኛ ፋንታ ሞቶአ ል፣ ከሙታንም ተነስቷል፣ በሰማያዊ ቤተ መቅደስ ስለ እኛ ለማገልገል አርጎአል፡፡ ሕዝቡን ለመጨረሻ ጊዜ ነፃ ለማውጣትና ሁሉን ነገር ወደ ቀድሞ ሁኔታው ለመመለ በክብር ዳግም ይመጣል፡ ፡ ( ዮሐ. 5፡ 22፣ ሉቃስ 1፡ 35፣ ፊል. 2፡ 5-11፣ እ ብ. 2፡ 9-18፣ 1ቆሮ. 15፡ 3፣ 4 ፣ ዕ ብ. 8፡ 1፣ 2፣ ዮሐ. 14፡ 1-3)፡ ፡

5.  እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ

ዘላለማዊ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በፍጥረት፣ መለኮት ሥጋ በመልበስና በደህንነት ሥራ ከአብና ከወልድ ጋር አብሮ ሰርቷል፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ ፀሐፊዎችን አነሳስቶአቸዋል፡፡ የክርስቶስን ሕይወት በኃይል ሞልቶአል፡፡ ሰብአዊ ፍጡራንን በመዝለፍ ወደ እግዚአብሔር ይመልሳል፣ ምላሽ የሚሰጡትንም በማደስ ወደ እግዚአብሔር አምሳል ይለውጣቸዋል፡ ፡ ሁልጊዜ ከልጆቹ ጋር እንዲሆን በአብና በወልድ ስለ ተላከ ለ ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ስጦዎችን ይሰጣታል፣ ከቅዱስ መጽሐፍት ጋር በተጣጠመ ሁኔታ ወደ እውነት ሁሉ ይመራታል ( ዘ ፍ. 1፡ 1፣ 2፣ ሉቃስ .1፡ 35፣ 4፡ 18፤ የ ሐዋ. 10፡ 38፣ 2ጴጥ. 1፡ 21፣ 2ቆ ሮ. 3፡ 18፣ ኤፌ.4፡ 11፣ 12፣ የ ሀ ዋ.1፡ 8፣ ዮሐ. 14፡ 16-18፣ 26፣ 15፡ 26፣ 27፣ 16፡ 7-13)፡ ፡

Gradient Blue Background

6 . ፍጥረት

እግዚአብሔር የሁሉም ነገር ፈጣሪ ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የመፍጠር ሥራውን እውነተኛ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ እግዚአብሔር በስድስት ቀን ‹‹ሰማይና ምድርን ›› በምድር ላይ ያሉትን ሕይወት ያላቸውን ነገሮች ሁሉ ፈጥሮ በዚያ የመጀመሪያው ሳምንት ሰባተኛው ቀን ላይ አረፈ፡፡ ስለዚህ እርሱ ለፈፀመው የፍጥረት ሥራ ቋሚ መታሰቢያ እንዲሆን ሰንበትን አቋቋመ፡፡ የመጀመሪያዎቹ ወንድና ሴት የፍጥረት ሥራው ዘውድ በመሆን በእግዚአብሔር አምሳል ተፈጠሩ፤ በዓለም ላይ ገዥነት ተሰጣቸው፡፡ የዓለም ፍጥረት በተፈፀመ ጊዜ የእግዚአብሔርን ክብር መናገር በሚችል ሁኔታ ‹‹እጅግ መልካም›› ነበ ር ( ዘ ፍ. 1፡ 2፣ ዘ ፀ . 20፡ 8-11፣ መዝ. 18፡ 1-6፣ 104፣ ዕ ብ. 11፡ 3)፡ ፡

7.  የሰው ተፈጥሮ

ወንድና ሴት የተፈጠሩት በእግዚአብሔር አምሳል፤ ግለሰብነታቸው ተጠብቆ ከማሰብና ከማድረግ ነፃነት ጋር ነበር ፡፡ ምንም እንኳን ነፃ ሆነው ቢፈጠሩም እያንዳንዳቸው በአካል፣ በአእምሮና በመንፈስ ሊከፋፈሉ የማይችሉ አንድ አካል ሆነው ለሕይወት፣ ለእስትንፋስ ና ለሁሉም ነገር በእግዚአብሔር የሚደገፉ ነበሩ፡፡ የመጀመሪያው ወላጆቻችን እግዚአብሔርን አልታዘዝ ባሉ ጊዜ በእርሱ ላይ የነበራቸውን መደገፍ ባለመቀበ ላቸው ምክንያት ከእግዚአብሔር በታች ከተሰጣቸው ከፍ ያለ ቦታ ወደቁ፡፡ ልጆቻቻው ይህን የወደቀ ተፈጥሮና ውጤቶቹን ይጋራሉ፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር በክርስቶስ ዓለሙን ከራሱ ጋር በማስታረቅ በመን ፈሱ አማካይነት ንስሐ በሚገቡ ሟች በሆኑ ሰዎች ውስጥ የፈጣሪያቸውን ምስል ይመልሳል፡፡ ለእግዚአብሔር ክብር ስለ ተፈጠሩ እርሱን እንዲወዱትና እርስ በእርሳቸው እንዲዋደዱ፣ ለአከባቢያቸውም እንዲጠነቀቁ ተጠርተዋል (ዘ ፍ.1፡ 26-28፣ 2፡ 7፣ መዝ. 8፡ 4-8 የ ሐዋ. 17፡ 24-28፣ ዘ ፍ. 3፣ መዝ. 51፡ 5፣ ሮሜ.5፡ 12-17፣ 2ቆ ሮ.5፡ 19-20፣ መዝ.51፡ 10፣ 1ዮሐ. 4፡ 7፣ 8፣ 11፣ 20፣ ዘ ፍ.2፡ 15)፡ ፡

8. ታላ ቁ ተጋድሎ

የእግዚአብሔርን ባህርይ፣ ሕጉንና በዓለማት ላይ ያለውን ሉአላዊነት በተመለከተ በክርስቶስና በሰይጣን መካከል ባለው ተጋድሎ ውስጥ ሰብአዊ ፍጡር ሁሉ ተካፋይ ነው፡፡ ይህ ተጋድሎ መነሻው ፍጡር የነበረው፣ ከምርጫ ነፃነት ጋር የተፈጠረው፣ ራሱን ከፍ ከፍ በማድረግ የእግዚአብሔር ጠላት የሆነው ሰይጣን ከፊሉን መላእክት ወደ አመጽ በመራ ጊዜ በሰማይ ነበር፡፡ አዳምና ሔዋንም ወደ ኃጢያት በመራቸው ጊዜ የአመጽን መንፈ ስ ወደዚች ምድር አ መጣ፡፡ ይህ የሰው ኃጢያት በሰው ውስጥ ያለው የእግዚአብሔር ምስል እንዲዛባ፣ የተፈጠረው ዓለም ሥርዓት እዲያጣና ዓለምን ባጥለቀለቀው የውኃ ጥፋት እንዲጠፋ አደረገ፡፡ ፍጥረት ሁሉ እየተመለከተ ይህቺ ዓለም የዓለማት ሁሉ ተጋድሎ መድረክ ሆነች፣ በዚህ ተጋድሎ ውስጥ ሕዝቡን ለማገዝ እንዲመሯቸው፣ እንዲጠብቋቸውና በደህንነት መንገድ ላይ እዲያቆያቸው መንፈስ ቅዱስና ታመኝ መላእክቱን ይልካ ል (ራዕ ይ 12፡ 4-9፤ ኢሳ . 14፡ 12-14 ሕዝ. 28፡ 12-18፣ ዘ ፍ. 3፣ ሮሜ 1፡ 19-32፣ 5፡ 12-21 ፣ 8፡ 19-22፣ ዘ ፍ. 6፡ 18፣ 2ጴጥ. 3፡ 16፣ 1ቆ ሮ. 4፡ 9፣ ዕ ብ፣ 1፡ 14)፡ ፡

9 . የክርስቶስ ሕይወት፣ ሞት እና ትንሳኤ

ክርስቶስ ለአባቱ ፈቃድ ፍጹም በመታዘዝ በኖረበት ሕይወት ስቃዩን ሞቱና ትንሳኤው በእምነት የእርሱን ስርየት የሚቀበሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖራቸውና ፍጥረት ሁሉ የፈጣሪን ዘላለማዊና ቅዱስ ፍቅር በተሻለ ሁኔታ እንዲያስተውሉ፣ ለሰብዓዊ ዘር ኃጢአት ስርዓት መሆን የሚችልን ብቸኛ መንገድ አዘጋጀ፡፡ ይህ ፍጹም የሆነ ስርዓት የእግዚአብሔርን ሕግ ቅዱስነትና የእርሱን በጸጋ የተሞላ በሕርይ ያሳያለ፣ እርሱ ኃጢአታችንን በመኮነን ይቅርታን ይሰጠናል፡፡ የክርስቶስ ሞት ሞትክ የሚሆንና የሚቤዝ፣ የሚያስታርቅና የሚለወጥ ነበር፡፡ የክርስቶስ ትንሳኤ እግዚአብሔር በክፋ ኃይሎች ላይ የተቀዳጀውን ድል በማወጅ ስርዓቱን ለሚቀበሉ ሁሉ በኃጢአትና በሞት ላይ የሚቀዳጁትን የመጨረሻ ድል ያረጋግጥላቸዋል፡፡ በፊቱ በሰማይና በምድር ላይ ያሉ ጉልበቶች ሁሉ የሚንበረከኩለትን የኢየሱስ ክርስቶስን ጌትነት ያውጃል፡ ፡ (ዮሐ 3፡ 16፣ ኢሳ .53፤ ጼጥ.22፡ 21፣ 22፣ 1ቆ ሮ 15፡ 3፣ 4፣ 4፣ 20-22፣ 2ቆ.5፡ 14፣ 15፣ 19-21፣ ሮሜ 1፡ 4፣ 3፡ 25፣ 4፡ 25፣ 8፡ 3፣ 1ዮሐ2፡ 2፣ 4፡ 10፣ ቆ ላ.2፡ 15፤ ፊል2፡ 6-11፡ ፡ )

10. የደህንነት ልምምድ

እግዚአብሔር በዘላለማዊው ፍቅሩና ምሕረቱ እኛ በእርሱ የእግዚአብሔር ጽድቅ እንሆን ዘንድ ኃጢአት የሚያውቀውን ክርስቶስን ስለ እኛ ኃጢአት እንዲሆን አደረገው፡፡ በመንፈስ ቅዱስ በመመራት ምን እንደሚያስፈልገን ይሰማናል፣ ኃጢአተኛነታችንን እንቀበላለን ለመተላለፋችን ንስሐ እንገባለን፣ ኢየሱስ ጌታና ክርስቶስ ፣ ምትካችንና ምሳሌያችን እንደሆነ አናምናለን፡፡ ይህ ደህነትን የሚቀበል እምነት በቃለ መለኮታዊ ኃይል የሚመጣ ሲሆን የእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ ነው፡፡ በክርስቶስ አማካይነት ጸድቀናል፣ የ ልጅነት ማዕረግን አግኝተናል ከኃጢአት ጌትነትም ነፃ ወጥተና፡፡ በመንፈስ አማካይነት እንደገና ተወልደን ተቀድሰናል፤ መንፈስ አእምሮአችንን ያድሳል፣ የእግዚአብሔርን የፍቅር ሕግ በልባችን ይጽፋል፣ ቅዱስ ሕይወትን እንድንኖር ኃይል ተሰጥቶናል፡፡ በእርሱ በመኖር የመለኮታዊ ባሕርይ ተካፋዮች እንሆናለን፣ አሁንም ሆነ በፍርድ ቀን የደህንነት ማረጋገጫም ይኖረና ል፡ ፡ (2ቆ ሮ.5፡ 17፤ የ ሐ.3፡ 16፤ ገ ላ .1፡ 41፤ 4፡ 4-7፤ ቲቶስ 17፡ 5፤ ዮሐ16፡ 8፤ ገ ላ .3፡ 13፣ 14፤ 1ጼጥ2፡ 21፣ 22፣ ሮሜ10፡ 27፣ ሉቃስ 17፡ 5፣ ማር 9፡ 23፣ 24 ኤፌ2፡ 5-10 ሮሜ3፡ 21-26፤ ቆላ 1፡ 13፣ 14፣ ሮሜ 8፡ 14-17፣ ገ ላ 3፡ 26፣ ዮሐ3፡ 3-8፣ 1ጼጥ.1፡ 23፣ ሮሜ12፡ 2፣ ዕ ብ 8፡ 7፣ 12 ሕዝ6፡ 25-27፣ 2ጼጥ.1፡ 3፡ 4፤ ሮሜ8፡ 1-4፤ 5፡ 6-10፡ ፡ )

11.  በክርስቶስ ማደግ

ኢየሱስ በመስቀል ሞቱ በክፉ ኃይሎች ላይ ድልን ተቀዳጀ፡፡ በምድራዊ አገልግሎቱ ወቅት ጋኔናዊ መናፍስት የተገዙለት ኢየሱስ ኃይላቸውን ሰብሯል፣ የመጨረሻ ጥፋታቸውንም እርግጠኛ አድርጓል፡፡ የኢየሱስ ድል ከእርሱ ጋር በሰላም፣ በደስታና በፍቅሩ በመተማመን ስንጓዝ ሳለ አሁንም ሊቆጣጠሩን እየፈለጉ ባሉ የክፋ ኃይሎች ላይ ድልን ለኢየሱስ እንደ አዳኝና ጌታ አድርገን ሁልጊዜ ራሳችንን ስንሰጥ ከዚህ በጨለማ፣ የክፋ ኃይላትን በመፍራት፣ በድንቁርና እና ከዚህ በፊት እንመላለስበት በነበረው ዓይነት ትርጉም የለሽ ሕይወት አንኖርም፡፡ እየተገናኘን፣ ቃሉን በመመገብ፣ በእርሱና እርሱ የሰጠንን በረከት በማሰላሰል፣ እርሱን በዝማሬ በማመስገን ለአምልኮ በመሰብሰብና የቤተክርስቲያንዋን ተልዕኮ በተግባራዊ ለማድረግ ተሳትፎ በማድረግ የእርሱን ባሕርይ ወደ መምሰል እንድናድግ ተጠርተናል፡፡ በፍቅር ስንመሰክር የእርሱ በመንፈሱ አማካይነት ሁልጊዜ መገኘት እያንዳንዷን ደቂቃና ተግባር ወደ መንፈሳዊ ልምምድ ይለውጠዋል፡ ፡ (መዝ1፡ 1-2፣ 23-4፣ 7፡ 11-12፣ ቆ ላ.1፡ 13-14፣ 2፡ 6፡ 14-15፣ ሉቃ10፡ 17-20፣ ኤፌ5፡ 19፣ 20፣ 6፡ 12 18፣ ተሰ5፡ 23፣ 2ጼጥ2፡ 9፣ 3፡ 18፣ 2ቆ ሮ3፡ 17 18፣ ፌል3፡ 7 14፣ ተሰ 5፡ 16-18፣ ማቴ20፡ 25-28፣ ዮሐ20፡ 21፣ ገ ላ 5፡ 22-25፣ ሮሜ8፡ 38-39፣ 1ዮሐ4፡ 4፣ እ ብ10-25)፡ ፡

Pastel Gradient Background

12.  ቤተክርስቲያን

ቤተክርስቲያን ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ ጌታና አዳኝ አድርገው የሚቀበሉ አማኞች የመሰረቱት ማህበረሰብ ነው፡፡ በብሉይ ኪዳን ዘመን ከነበረው የእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር ቀጣይነት ባለው ሁኔታ ከዓለም ተጠርተናል፤ ለአምልኮ፣ ክርስቲያናዊ ህብረት ለመፍጠር፣ የቃል ትምህርት ለማግኘት የጌታን ራት ለመካፈል ሰብዓዊ ዘርን በሙሉ ለማገልገልና ወንጌልን ለዓለም ሁሉ ለማወጅ አንድነት እንፈጥራለን፡፡ ቤተክርስቲያን ስልጣንዋን ያገኘችው ከክርስቶስ፣ ስጋ ለብሶ ከተገለጠው ቃልና ከተፃፈው ቃል፣ ከመጽሐፍ ቅዱስ ነው፡፡ ቤተክርስቲያን የእግዚአብሔር ቤተሰብ ነች፡፡ አባላቱ ከእርሱ የልጅነትን መብት በማግኘት በአዲስ ኪዳን መሰረት ይኖራሉ። ቤተክርስቲያን ክርስቶስ  እራሱ ራስ የሆነበት የእምነት ማህበረሰብና የክርስቶስ አካል ነች፡፡ ቤተክርስቲያን ክርስቶስ ሊቀድሳትና ሊያነፃት የሞተላት ሙሽራ ነች፡፡ ክርስቶስ ዳግም በአሸናፊነት ሲመለስ እርስዋን በግርማ የተሞላች ቤተክርስቲያን፣ በዘመናት ሁሉ ታማኝ የሆነች፣ በደሙ የተገዛች፣ ነቁጣና የፊት መጨማደድ የሌለባት፣ ነገር ግን ቅድስትና ነውር የለሽ አድርጎ ለራሱ ያቀርባ ታል፡ ፡ (ዘ ፍ12፡ 3፣ የ ሐዋ 7፡ 38፣ ኤፌ 4፡ 11-15፣ 3፡ 8-11፣ ማቴ 28፡ 19-20፣ 16፡ 13- 20፤ 18፡ 18፣ ኤፌ2፡ 19-22፣ 1፡ 22-23፣ 5፡ 23-27፣ ቆ ላ1፡ 17-18)፡ ፡

13.  ቅሬታዋና ተልዕኮዋ

ዓለም አቀፋዊ ቤተክርስቲያን ከእውነተኛ ልባቸው በክርስቶስ የሚያምኑትን ሁሉ ታጠቃልላች፣ ነገር ግን ከህደት በተስፋፋበት በመጨረሻ ዘመን ቅሬታዎቹ የእግዚአብሔርን ትዕዛዛትና የኢየሱስን ኃይማኖት እንዲጠብቁ ተጠርተዋል፡፡ ይህቺ ቅሬታ የፍርድ ሰዓት መድረሱን ታስታውቀለች፡፡ ይህ አዋጅ በራዕይ 14 ላይ በተገለፀው በሶስቱ መላእክት መልእክት ተመስሏል፡፡ ይህ መልእክት በሰማይ የተሐድሶን ስራ ያስከትላል፡፡ በዚህ ዓለም አቀፋዊ ምስክርነት እያንዳንዱ አማኝ የግል ድርሻ እንዲኖረው ተጠርቷል፡ ፡ (ራዕ ይ 12፡ 17፣ 14፡ 6-12፣ 18፡ 1- 4፣ 2ቆ ሮ5፡ 10፣ ይሁዳ3፣ 14፣ 1ጼጥ.1፡ 16-19፣ 2ጼጥ 3፡ 10-14፣ ራዕ ይ21፡ 1-14)

14.  አንድነት በክርስቶስ አካል ውስጥ

ቤተክርስቲያን ከሕዝብ፣ ከነገድ  ቋንቋና ከወገን ሁሉ የተጠሩ ብዙ አባላት ያሉባት አንድ አካልናት፡፡ እኛ በክርስቶስ አዲስ ፍጥረት ነን፣ የዘር፣ የባህል፣ የትምህርትና የዜግነት ልዩነቶች፣ በትልቅና በትንሽ፣ በድሃና በሐብታም፣ በወንድና በሴት መካከል ያሉ ልዩነቶች ሊከፋፍሉን ይገባም፡፡ በአንድ መንፈስ ከራሱ ጋር እና ከእርስ በርሳችን ጋር ወደ አንድ ህብረት ባስተሳሰረን በክርስቶስ ሁላችንም እኩል ነን፡፡ ያለ አድልዎና ያለ መቆጠብ ማገልገልና መገልገል አለብን፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በገለጠልን መገለጥ አንድ እምነትና ተስ ፋን እንጋራለን፣ በአንድ ምስክርነትም ሁሉን እንደርሳለን፡፡ ይህ አንድነት ምንጩ እንደ ልጆቹ አድርጎ በቀበለን በስላሴ መካከል ያለው አንድነት ነው፡ ፡ (ሮሜ 12፡ 4፡ 5፣ 1ቆሮ 12፡ 12-14፣ ማቴ 28፡ 19-20፣ መዝ 133፡ 2፣ 2ቆ ሮ 5፡ 166-17፣ የ ሐዋ 17፡ 26፣ 27፣ ገ ላ 3፡ 27፣ 29፣ ቆ ላ 3፡ 10-15፣ 4፡ 14- 16፣ 4፡ 16፣ ዮሐ17፡ 20-23)፡፡

15.  ጥምቀት

በጥምቀት በኢየሱስ ክርስቶስ ሞትና ትንሳኤ ያለንን እምነት እንገልጻለን፣ ለኃጢአት መሞታችንና በአዲስ ሕይወት የመመላለስ ዓላማንም እንመሰክራለን፡፡ ስለዚህ ክርስቶስ ጌታና አዳኝ መሆኑን፣ የእርሱ ሕዝብ መሆናችንን፣ በእርሱ ቤተክርስቲያንም እንደ አባል ተቀባይነት ማግኘታችንን እንገልፃለን፡፡ ጥምቀት ከክርስቶስ ጋር አንድ የመሆናችን፣ ለኃጢአቶቻችን ይቅርታ የማግኘታችን እና መንፈስ ቅዱስን የመቀበላችን ምልክት ነው፡፡ ጥምቀት የሚፈፀመው በውኃ በመጥለም ነው፣ ይህም በኢየሱስ ላይ ያለውን እምነት በማጽናት ላይ የሚደገፍና ለኃጢአት የመናዘዝ ማረጋገጫ ነው፡፡ ጥምቀት ቅዱሳ ጽኁፎችን መማርንና የእርሱን አስተምህሮ መቀበልን ተከትሎ የሚመጣ ነው፡ ፡ (ሮሜ 6፡ 1-6፣ ቆላ 2፡ 12፣ 13፣ የ ሐዋ 16፡ 30-33፣ 22፡ 16፣ 2፡ 38፣ ማቴ28፡ 19፣ 20)፡ ፡

16.  የጌታ ራት

የጌታ ራት ጌታችን አዳኛችን በሆነው በእርሱ ላለን እምነት መግለጫ እንዲሆን የአካሉና የደሙ ምሳሌ በሆነው አገልግሎት መሳተፍ ነው፡፡ በዚህ የጌታ ራት አገልግሎት ልምምድ ውስጥ ክርስቶስ ሕዝቡን ለመገናኘትና ብርታት ለመስጠት ይገኛል። በዚህ ስነስርዓት ስንሳተፍ እርሱ እንደገና እስኪመጣ ድረስ የጌታን ሞት በደስታ እናውጃለን። ለጌታ ራት መዘጋጀት ራስን መመርመርን፣ ንስሐና ኑዛዜን ያጠቃልላል፡፡ ጌታ የእግር እጥበት አገልግሎትን የሰጠው በዚህ ሁኔታ መንፃትን፣ የክርስቶስን በመሰለ ራስን ዝቅ ማድረግ እርስ በርሳችንን ለመገልገል ፈቃደኛ መሆናችን ለመግለጽና ልቦቻችንን በፍቅር አንድ ለማድረግ ነው፡፡ የጌታ ራት አገልግሎት ለሚያምኑ ክርስቲያኖች ሁሉ ክፍት ነው፡፡ (1ቆ ሮ10፡ 16፡ 17፡ 11፡ 23-3፣ ማቴ 26፡ 17-30፣ ራዕ ይ 3፡ 20፡ ዮሐ 6፡ 48-63፣ 13፡ 1-17)፡ ፡

Gradient Background

17.  መንፈሳዊስ ጦታዎችና አገልግሎቶች

እግዚአብሔር እያንዳንዱ አባል ለቤተክርስቲያኑና ለሰብአዊ ዘር የጋራ ጥቅም ስራ ላይ ሊያውላቸው የሚገባቸው መንፈሳዊ ስጦታዎች በየዘመኑ ላሉ የእርሱ ቤተክርስቲያን አባላት ሁሉ ይሰጣል፡፡ ለእያንዳንዱ ሰው እንደሚፈልገው በሚያካፍለው በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት የተሰጡት እነዚህ ስጦታዎች ለቤተክርስቲያን በመለኮት የተሰጧትን ተግባራት ለማሟላት እንድትችል የሚያስ ፈልጉ ችሎታዎችንና አገልግሎቶችን ይሰጣል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚገልጸው እነዚህ ሥጦታዎች እንደ እምነት፣ መፈወስ፣ ትንቢት፣ መናገር፣ መስበክ፣ ማስተማር፣ ማስተዳደር፣ ማስታረቅ፣ ርህራሄ፣ ራስን መስዋዕት የሚያደርግ አገልግሎትና፣ ሰዎች ለመርዳትና ለማበረታታት የሚያስችሉ የበጎ አድርጎት ስራዎችን ያጠቃልላ ል፡፡ አንዳንዱ አባላት በእግዚአብሔር ተጠርተው በተለየ ሁኔታ አባላትን ለአገልግሎት ለማስታጠቅ፣ ቤተክርስቲያንን ወደ መንፈሳዊ ብስለት ደረጃ ለማድረስና የእምነት አንድነትንና እግዚአብሔርን ማወቅን ለማጎልበት በሚያስፈልጉ ቤተክርስቲያን በምታውቃቸው በእረኝነት በወንጌላዊነት በሐዋርያነትና በማስተማር አገልግሎቶች ማገልገል እንዲችሉ መንፈስ ተሰጥቷቸዋል፡፡ አባላት እነዚህን መንፈሳዊስ ጦታዎች እንደ እግዚአብሔር ልዩ ልዩ ፀጋ ታማኝ መጋቢዎች ስራ ላይ በሚያውሉበት ጊዜ ቤተክርስቲያን አጥፊ ከሆነው የሐሰት አስተምህሮ ተጽእኖ ነፃ ትሆናለች፣ ከእግዚአብሔር የሆነ እድገትን ታድጋለች በእምነትና በፍቅርም ትገነባለች፡፡ (ሮሜ 12፡ 4-8፣ ቆሎ 12፡ 19-11፣ 27፣ 28፣ ኤፌ4፡ 8፡ 11-16፣ የ ሐዋ6፡ 17፣ 1ጢሞ3፡ 1-13፣ 1ጼጥ4፡ 10፣ 11)፡ ፡

18.  የትንቢት ስጦታ

ከመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች አንዱ ትንቢት ነው፡፡ ይህ ስጦታ ቅሬታዎችን ከሌሎች የሚለይ ምልክት ሲሆን በኤሌን ጂ ዋይት አገልግሎት ውስጥ ታይቷል፡፡ እንደ እግዚአብሔር አገልጋይ የእርሷ ጽሁፎች ለቤተክርስቲያን መጽናናትን፣ አመራርን፣ ትምህርትንና ተግሳጹን የሚሰጡ ቀጣይነትና ስልጣን ያላቸው የእውነት ምንጮች ያለበት መስፈርት መሆኑንም ግልጽ ያደርጋሉ፡፡ (ኢዮኤል 2፡ 28፣ 29፤ የ ሐዋ2፡ 14-21፣ አ ብ1፡ 1-3፤ ራዕ ይ12፡ 7፣ 19-10)፡ ፡

19.  የእግዚአብሔር ሕግ

የእግዚአብሔር ታላላቅ መርሆዎች ተጨባጭ የሆኑት በአስርቱ ትዕዛዛት ውስጥ ሲሆን በምሳሌያዊ ሁኔታ የተገለጹት ደግሞ በክርስቶስ ሕይወት ውስጥ ነው፡፡ ሰብዓዊ ባህርይንና ግንኙነቶችን በተመለከተ የእግዚአብሔርን ፍቅር፣ ፈቃድና ዓላማ የሚገልጹ ሲሆን በየዘመኑ ባሉ ሰዎች ሁሉ የግድ መጠበቅ ያለባቸው ናቸው፡፡ እነዚህ ደንቦች እግዚአብሔር ከህዝቡ ጋር ስላለው ቃል ኪዳን መሰረትና የእግዚብሔርን ፍርድ መመዘኛ ናቸው፡፡ በመንፈስ ቅዱስ አማካ ይነት ኃጢአትን በማመልከት አዳኝን የመፈለግ ስሜት ይቀሰቅሳሉ፡፡ ደህንነት ሙሉ በሙሉ በጸጋ እንጂ በስራ አ ይገኝም፣ ነገር ግን የፀጋ ፍሬ ለትዕዛዛት መታዘዝ ነው፡፡ ይህ መታዘዝ የክርስቲያን ባሕርይን በማጎልበት የደህንነት ስሜትን ይፈጥራል፡፡ ለእግዚአብሔር ስላለን መታዘዝ ሕይወትን ለመለወጥ የክርስቶስን ኃይል ስለሚያሳይ የክርስቲያን ምስክርነትን ያጠናክራል፡፡ (ዘ ፀ 20፡ 1-17፣ ፤ ፣ አ ረ 40፡ 7፣ 8፣ ማቴ22፡ 36-40፣ ዘ ዳ28፡ 1- 14፤ ማቴ5፡ 17-20፣ ዕ ብ8፡ 8-10ዮሐ15-7-10ኤፌ2፡ 8-10፤ ዮሐ5፡ 3፣ ሮሜ8፡ 3፣ 4፤ መዝ19፡ 7-14)፡ ፡

15.  ጥምቀት

በጥምቀት በኢየሱስ ክርስቶስ ሞትና ትንሳኤ ያለንን እምነት እንገልጻለን፣ ለኃጢአት መሞታችንና በአዲስ ሕይወት የመመላለስ ዓላማንም እንመሰክራለን፡፡ ስለዚህ ክርስቶስ ጌታና አዳኝ መሆኑን፣ የእርሱ ሕዝብ መሆናችንን፣ በእርሱ ቤተክርስቲያንም እንደ አባል ተቀባይነት ማግኘታችንን እንገልፃለን፡፡ ጥምቀት ከክርስቶስ ጋር አንድ የመሆናችን፣ ለኃጢአቶቻችን ይቅርታ የማግኘታችን እና መንፈስ ቅዱስን የመቀበላችን ምልክት ነው፡፡ ጥምቀት የሚፈፀመው በውኃ በመጥለም ነው፣ ይህም በኢየሱስ ላይ ያለውን እምነት በማጽናት ላይ የሚደገፍና ለኃጢአት የመናዘዝ ማረጋገጫ ነው፡፡ ጥምቀት ቅዱሳ ጽኁፎችን መማርንና የእርሱን አስተምህሮ መቀበልን ተከትሎ የሚመጣ ነው፡ ፡ (ሮሜ 6፡ 1-6፣ ቆላ 2፡ 12፣ 13፣ የ ሐዋ 16፡ 30-33፣ 22፡ 16፣ 2፡ 38፣ ማቴ28፡ 19፣ 20)፡ ፡

20.  ሰንበት

በጎ የሆነው ፈጣሪ ከስድስት የፍጥረት ቀናት በኃላ በሰባተኛው ቀን አርፎ ለሰዎች ሁሉ ሰንበትን እንደ የፍጥረት መታሰቢያ አቋቋመ፡፡ የእግዚአብሔር የማይለወጠው ሕግ አራተኛው ትዕ ዛዝ ይህን ሰባተኛውን ቀን ሰንበትን የሰንበት ጌታ ከሆነው ከኢየሱስ ትምህርትና ልምምድ ጋር በተጣጣመ ሁኔታ የእረፍት፣ የአምልኮና የአገልግሎ ቀን በማድረግ እንድን ጠብቅ ይጠይቃል፡፡ ሰንበት ከእግዚአብሔርና ከእርስ በርስ ጋር አስደሳች የሆነ ግንኙነት የመንፈጥርበት ቀን ነው፡፡ ሰንበት በክርስቶ የመዳናችን ምልክት፣ የመቀደሳችን ምልክት የታማኝነታችን ምልክት እና ወደፊት በእግዚአብሔር መንግስት የምንኖረው ዘላለማዊ ሕይወት ቅምሻ ነው፡፡ ሰንበት በእርሱና በሕዝቡ መካከል ያለው የእግዚአብሔር ዘላለማዊ ኪዳን ዘላቂ ምልክት ነው። ይህንን የተቀደሰ ጊዜ ከምሽት እስከ ምሽት፣ ከፀሀይ ግባት እስከ ፀሐይ ግባት፣ በደሰታ መጠበቅ የእግዚአብሔር የፈጣሪነትና የአዳኝነት ስራን ማክበር ነው፡፡ (ዘ ር 2፡ 13፤ ዘ ጸ20፡ 8 11፤ ሉቃስ 4፡ 16፤ ሕዝ20፡ 12፣ 20፤ ኢሳ 56፡ 5፣ 6፤ 58፡ 13፣ 1 4፤ ማቴ12፡ 1፣ 12፣ ዘ ጸ 31፡ 13 17፤ ዘ ጸ 5፡ 12፣ 15፤ እ ብ.4፡ 1 11፣ ዘ ሌ23፡ 32፤ ማር1፡ 32)፡ ፡

21.  መጋቢነት

እግዚአብሔር ጊዜና እድሎችን፣ ችሎታና ሐብትን፣ የምድርን በረከቶችና ሐብቶችዋን የሰጠን የእርሱ መጋቢዎች ነን፡፡ እነርሱን በአግባቡ ስለመጠቀማችን በእግዚአብሔር ዘንድ ኃላፊነት አለብን፡፡ እርሱንና መሰሎቻችንን በታማኝነት በማገልገል፣ የእርሱን ወንጌል ለማወጅና ቤተክርስቲያንንና እድገትዋን ለመደገፍ አስራትን በመመለስና ስጦታን በመስጠት የእግዚአብሔርን ባለቤትነት እንገልጻለን፡፡ መጋቢትን በፍቅር በመመገብና በራስ ወዳድነትና በምኞት ላይ ድልን እንድንቀዳጁ በእግዚአብሔረ የተሰጠን እድል ነው፡፡ መጋቢ ከእርሱ ታማኝነት የተነሳ ለሌሎ በሚመጡ በረከቶች ይደሰታል። (ዘ ረ ፍ1፡ 26-28፤ ማቴ23፡ 231፣ 2ቆ ረ8፡ 1-15፣ ሮሜ15፡ 26፣ 27)፡ ፡

22.  የክርስቲያን ባሕርይ

የተጠራነው የምናስብ የሚሰማንን እና የምናደርገውን ነገር ከሰማይ መርሆዎች ጋር በተጣጣመ ሁኔታ እንድናደርግ እግዚአብሔርን የምንመስል ሕዝብ እንድንሆን ነው፡፡ መንፈስ በውስጣችን የጌታችንን ባሕርይ እንደ ገና እንዲፈጥር በሕይወታችን ክርስቶስን የሚመስል ንጽህና፣ ጤና ፣ እና ደስታ ሊፈጥሩልን በሚችሉ ነገሮች ላይ ብቻ ራሳችንን እናሳትፋለን፡፡ ይህ ማለት የምንዝናናበትና ደስታን የምንፈልግበት መንገድ ክርስቲያናዊ ለዛና ውበት የሚጠይቃቸውን ከፍ ያሉ መስፈርቶች የሚያሟላ መሆን አለበት፡፡ የባህል ልዩነቶችን ከግንዛቤ ውስጥ ብናስገባም፣ አለባበሳችን ቀላል፣ ጨዋነትን የተላበሰ፣ ንጹህ፣ እና እውነተኛ ውበታችን ውጫዊ ማጌጥን ሳይሆን በውስጣቸው የማይጠፋውን የዋህና የዝግተኛ መንፈስ ጌጥን የለበሱትን የሚገጥም መሆን አለበት፡፡ በሌላ አነጋገር ደግሞ አካሎቻችን የመንፈስ ቅዱስ ቤተመቅደስ ስለሆኑ ማስተዋል ባለበት ሁኔታ ልንጠነቀቅላቸው ይገባል፡፡ ከበቂ የአካል እንቅስቃሴና እረፍት ጋር በተቻለ መጠን እጅግ ጤናማ የሆነ አመጋገብን ልንለማመድና በመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ ከተጠቀሱት ንጹህ ካልሆኑ ምግቦ ች መታቀብ አለብን፡፡ አስካሪ መጠጦችን፣ ትንባሆ እና ኃላፊነት በጎደለው ሁኔታ አደንዛዥ እጾችንና እነቃቂዎችን መጠቀም ለአካላችን ጎጂ ስለሆነ ከእርሱም መታቀብ አለብን፡፡ በዚህ ፈንታ አስተሳሰባችንና አካላችንን የእኛን ምሉእነት፣ ደስታ እና መልካምነት ወደሚፈልገው ወደ ክርስቶስ ስነ ስረዓ ት ሊያመጣ በሚችል በማንኛውም ነገር መጠመድ አለብን ፡ ፡ (ሮሜ12፡ 1፣ 2፤ 1ዮሐ2፡ 6፣ ኤፎ5፡ 1 21ፌል4፡ 8፤ 2ቆ ሮ10፡ 51፤ 6፤ 14- 17፤ 1ጼጥ3፡ 1-4፤ 1ቆ ሮ6፡ 19፣ 20፣ 10፣ 31፣ ሌዋ11፡ 47፤ 3ዮሐ2)፡ ፡

23.  ጋብቻና ቤተሰብ

ጋብቻ በመለኮት የተመሰረተው በኤድን ገነት ሲሆን ኢየሱስም በወንድና በሴት መካከል በፍቅር ጓደኝነት ለእድሜ ልክ አብረው የሚኖሩበት እንድነት መሆኑን አረጋግጦአል፡፡ ለክርስቲያን የጋብቻ ቃል ኪዳን ለእግዚአብሔርና ለትዳር አጋሩ ስለሆነ ተመሳሳይ እምነት ባላቸው ጓደኛሞች መካከል ብቻ ቅድስና፣ ቅርበት እና ዘላቂነት ማንጸባረቅ ያለበት ይህ ግንኙነት የተሰራው ከጋራ ፍቅር፣ ክብር መከባበርና ኃላፊነት ነው፡፡ ፍቺን በተመለከተ በዝሙት ምክንያት ካልሆነ በስተቀር ሚስቱን ፈትቶ ሌላይቱን የሚያገባ ሰው እንደሚያመነዝር ኢየሱስ አስተምሮአል፡፡ ምንም እንኳን አንዳንድ ቤተሰባዊ ግንኙነቶች መሆን ከሚገባቸው በታች ቢሆኑም በክርስቶስ አንዳቸው ለሌላቸው ራሳቸውን ሙሉ በሙሉ የሚሰጡ የትዳር አጋሮች በመንፈስ ቅዱስ ምሪትና በቤተክርስቲያ እንክብካቤ የፍቅር አንድነትን ሊያገኙ ይችላሉ፡፡ እግዚአብሔር ቤተሰብን ይባርካል እርስ በእርሳቸውም በመረዳዳት  ወደ ሙሉ ብስለት ለማደግ እንዲደርሱ ይፈልጋል፡፡ ወላጆች ልጆቻቸው እግዚአብሔርን እንዲወዱና እንዲታዘዙ በማስተማር ማሳደግ አለባቸው፡፡ በሕይወት ምሳሌነታቸውና በቃላቶቻቸው ክርስቶስ በፍቅር የሚቀጣ ገር እና ርህሩህ የአካል ክፍሎቹና የእግዚአብሔር ቤተሰብ እንዲሆኑ የሚፈልግ መሆኑን ማስተማር አለባቸው፡፡ የቤተሰብን ቅርበት መጨመር ከመጨረሻው የወንጌል መልእክት መለያዎች አንዱ ነው፡፡ (ዘ ፍ2፡ 18- 25፣ ማቴ19፡ 3 9ዮሐ2፡ 1 11፣ 1ቆሮ6፡ 14፣ ኤፎ5፡ 21 33፤ ማቴ5፡ 31፣ 32፣ ማር10፡ 11፡ 12ሉቃስ 16፡ 18.1ቆ ሮ፡ 1 0፣ 11፣ ዘ ጸ20፡ 12፣ ኤፌ6፡ 1-4፣ ዘ ጸ 6፡ 5-9ምሳ ሌ 22፡ 6፣ ሚል4፡ 5፣ 6)፡ ፡

Pastel Gradient Background

24.  የክርስቶስ አገልግሎት በሰማያዊው ቤተ መቅደስ

በሰማይ ሰው ሳይሆን እግዚአብሔር የተከለው እውነተኛ ቤተመቅደስ አለ፡፡ በዚያ ውስጥ ክርስቶስ ስለ እኛ አንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በመስቀል ላይ የሰጠውን የስርዓት መስዋት ጥቅሞች አማኞች እንዲያገኙት በማድረግ ያገለግላል፡፡ እንደ እኛ ሊቀካህን በመሾም የማማለድ አገልግሎቱን ወደ ሰማይ ባረገ ጊዜ ጀመረ፡፡በ1844 ዓ.ም፣ በ2300 ትንቢታዊ ቀናት መጨረሻ ላይ የማስተሰረይ አገልግቱ 2ኛውና የመጨረሻው ክፍል ገባ፡፡ በጥንቱ የዕብራውያን ቤተ መቅደስ የስርዓት ቀን አገልግሎት የተመሰለው ኀጢያት ሁሉ ለመጨረሻ ጊዜ የማጥፋት አካል የሆነው የፍርድ ምርመራ ስራ ነው፡፡ በዚያ ምሳሌያዊ በሆነው አገልግሎቱ ቤተ መቅደሱ የ ሚነጸው በእንስሳ መስዋዕቶች ነበር። ነገር ግን ሰማያዊው ከሞቱት መካከል እነማን በክርስቶስ እንዳቀላፍና በእርሱ አማካይነት በመጀመሪያው ትንሳኤ እንዲካፈል የተገቡ መሆናቸውን ለሰማያዊ አካላት ያሳል፡፡ በሕይወት ካሉትም እነማን በክርስቶስ እየኖሩ እንደ ሆኑና የእግዚአብሔርን ትዕዛዛትና የኢየሱስን እምነት በመጠበቅ በእርሱ ወደ ዘላለም መንግሰቱ ለመነጠቅ ዝግጁ እንደሆኑ ግልጽ ያደርጋል፡፡ ይህ ፍርድ በኢየሱስ የሚያምኑትን በማዳን የእግዚአብሔርን ፍትህ ያረጋግጣል፡፡ ለእግዚአብሔር ታማኝ የሆኑ መንግስትን እንደሚቀበሉ ይገልጻል፡፡ የክርስቶስ ይህን አገልግሎ መጨረስ ከዳግም ምጻቱ በፊት ለሰው ዘር የምህረት ደጅ መዘጋቱን ያመለክታል። (ዕ ብ8፡ 1-8፣ 4፡ 14-16፤ 9፡ 11- 22፣ 2፡ 6፡ 17፣ ዳን 7፡ 9 27፤ 8፡ 13፣ 14፣ 9፡ 27 27ዘ ሁ14፡ 34፣ ሕዝ47፡ 6፡ ዘ ሌ16፣ ራዕ ይ14፡ 6፡ 7፣ 20፡ 12፣ 14 ፣ 12፣ 22፡ 12)፡፡

25.  የክርስቶስ ዳግም ምጻት

የክርስቶስ ዳግም ምጻት የቤተክርስቲያንዋ የተባረከ ተስፋ የወንጌል የተከበረ ፍጻሜ ነው፡፡ የአዳኙ መምጣት ፊት ለፊት በአካል እየታየ እና ዓለም ዓቀፋዊ ሆኖ ነው፡፡ እርሱ ዳግም ሊመጣ ጻድቃን ሙታን ይነሱና በሕይወት ካሉት ጻድቃን ጋር ይከብሩና ወደ ሰማይ ይወሰዳሉ፣ ነገር ግን ኃጢአተኞች ይሞታሉ፡፡ የአብዛኞቹ ትንቢቶች መፈጸም ከአሁኑ የአለም ሁኔታ ጋር በመጣመር የክርስቶስ ዳግም ምጻት የማይቀር መሆኑን ያመለክታል፡፡ ያክስተት የሚሆንበት ጊዜው ስላልተገለጠልን ሁልጊዜ የተዘጋጀን እንድንሆን ማሳሰቢያ ተሰጥቶና፡፡ (ቲቶ 2፡ 13፣ ዕ ብ9፡ 28፣ ዮሐ14፡ 1- 31የ ሐዋ1፡ 9-11፣ ማቴ24፡ 14፣ ራዕ ይ1፡ 7 ማቴ 24፡ 43፣ 44 1ተሰ 4፡ 13-18፣ 1ቆ ሮ 15፡ 51-54፣ 2ተሰ 1፡ 7-10፣ 2፡ 8፣ ራዕ ይ14፡ 14-20፣ 19፣ 11-21፣ ማቴ24፣ ማር13፣ ሉቃስ21፣ 2ጢሞ3፡ 1-5፣ 1ተሰ 5፡ 1- 6)፡ ፡

26.  ሞትና ትንሳኤ

የኃጢአት ደሞዝ ሞት ነው፡፡ ነገር ግን ብቻውን የማይሞት እግዚአብሔር ለዳኑት የዘላለም ሕይወት ይሰጣል፡፡ እስከዚያ ቀን ድረስ ሞት ሁሉም ሰዎች ምንም ነገር ሳያውቁ የሚቆዩበት ሁኔታ ነው፡፡ ሕይወታችን የሆነው ክርስቶስ ሲገለጥ ከሙታን የተነሱት ጸድቃንና በሕይወት የነበሩት ጻድቃን ከብረው ጌታቸውን ለመገናኘት ይነጠቃሉ፡፡ የኃጢአተኞች ትንሳኤ የሆነው ሁለተኛው ትንሳኤ ከሺህ ዓመት በኃላ ይሆናል፡፡ (ሮሜ 6፡ 23፣ 1ጢሞ 6፡ 15፣ 16፣ መከ9፡ 5፣ 6፣ መዝ146፡ 41፣ ዮሐ11፡ 11-14፣ ቆ ላ 3፣ 4፣ 1ቆሮ15፡ 154፣ 1ተሰ 4፡ 3፡ 17፣ ዮሐ5፡ 28-29፣ ራዕ ይ20፡ 1-10)፡ ፡

27.  ሺህ ዓመትና የኃጢአት ፍጻሜ

ሺህ ዓመት በመጀመሪያውና በሁለተኛው ትንሳኤዎች መካከል ባለው ጊዜ ውስጥ ክርስቶስ ከቅዱሳኑ ጋር በሰማይ የሚነግስበት ጊዜ ነው፡፡ በዚህን ጊዜ ኃጢተኞች ሙታን ይፈረዳሉ፣ ምድር ሕያዋን ሰዎች የማይኖሩበት ባድማ ትሆናለች፣ ነገር ግን ሰይጣንና መላእክቱ ይኖሩበታል፡፡ በሺህ ዓመት ማብቂያ ላይ ክርስቶስ ከቅዱሳኑ ና ከቅድስቲቱ ከተማ ጋር ከሰማይ ወደ ምድር ይወርዳል፡፡ ያኔ ኃጢአተኛ ሙታን ይነሱና ከሰይጣንና ከመላእክቱ ጋር ከተማዋን ይከባሉ፡፡ ነገር ግን እሳት ከእግዚአብሔር ዘንድ ወርዳ በመብላት ምድርን ታነጻለች፡፡ ከዚያ በኃላ ዩኒቨርስ ከኃጢአትና ኃጢተኞች ለዘላለም ነጻ ይወጣል፡፡ (ራዕ ይ 20፡ 11 1ቆ ሮ 6፡ 2፡ 3 ኤር 4፡ 23-26፣ ኤር 4፡ 23- 26፣ ራዕ ይ 21፡ 1-5፣ ሚል 4፡ 11 ሕዥ 28፡ 19፡ 20)፡ ፡

28.  አዲሲቱ ምድር

ቅዱሳን በሚኖሩበት አዲሲቱ ምድር እግዚአብሔር ለዳኑት ዘላለማዊ ቤትና በፊቱ የዘላለም ሕይወት፣ ፍቅር ደስታ እና ትምህርት የሚያገኙትን ፍጹም አካባቢ ይሰጣቸዋል፡፡ በዚህ ቦታ እግዚአብሔር እራሱ ከሕዝቡ ጋር ይኖራል፣ ስቃይና ሞት ይጠፋሉ፡፡ ቃላቁ ተጋድሎ ይጠናቀቃል፣ ከዚያ በኃላ ኃጢአት አይኖርም፡፡ ሁሉም ነገር ሕይወት ያለውም ሆነ ሕይወት የሌለው እግዚአብሔር ፍቅር መሆኑን ያውጃል፣ እርሱ ለዘላለም ይነግሳል፡፡ (2ጼጥ3፡ 13፣ ኢሳ 35፡ 65- 17-25፣ ማቴ5፡ 5፣ ራዕ ይ21፡ 1-7፣ 22፡ 1-5፣ 11፡ 15)፡ ፡

bottom of page